በሚቀጥለው ሳምንት መጋቢት 4 በደቡብ አፍሪካው ማሜሎዲ ሰንዳውንስ እና በግብፁ አል አህሊ መካከል የሚደረገዉን ተጠባቂ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እንደሚመራዉ ታዉቋል።
ከ33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ መልስ በተመሳሳይ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሞሮኮው ራጃ ካዛብላንካ ከደቡብ አፍሪካው አማዙሉ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ ከድንቅ ብቃት ጋር መምራቱ ይታወሳል።