ከሱዳኑ ኤልሜሬክ ክለብ ጋር በስምምነት ተለያይተው ወደታነዛኒያው ሲምባ ያመሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና አሰልጣኝ ፈረንሳያዊው ዲዲዬ ጎሜስ ከተከታያቸው ያንግ አፍሪካንስ በ9 ነጥቦች ርቀው የታንዛኒያ ሻምፒዮና ሆነዋል፡፡
ዲዲዬ ጎሜስ በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ደርሰው በደቡብ አፍሪካው ክለብ ካይዘር ቺፍስ በድምር 4-3 ተሸንፈው ከውድድር መውጣታቸው ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ ቡናን ጨምሮ በኢትዮጵያ፣ በግብጽ፣ በጊኒና በሱዳን ያለዋንጫ የቆዩት ፈረንሳያዊው አሰልጣኝ በመጨረሻም ተሳክቶላቸው ሻምፒዮን በአስተማማኝ ሁኔታ አሳክተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ዲዲዬ ጎሜስ ከኢትዮጵያ ቡና በተጨማሪ በሩዋንዳ፣ በካሜሮን ሻምፒዮን የነበሩ ሲሆን በኢትዮጵያም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫን አሸንፍ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ ከሲምባ ጋር ያነሱት ዋንጫ በአህጉሪቱ የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ ያሳኩት ሰባተኛ ዋንጫ ሆኖ ተመዝግቦላቸዋል፡፡