የፋሲል ከነማው የፊት መስመር ተጫዋች አማኑኤል ገብረሚካኤል ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ካራቀው ጉዳት አገግሞ ወደ ጨዋታ ለመመለስ መቃረቡ ተዘግቧል።
ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ እንዳደረገው መረጃ ከሆነ ተጫዋቹ በነገው ዕለት ከቡድኑ ጋር ልምምድ ማድረግ ይጀምራል። በ2015 ዓ.ም የዝውውር መስኮት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን የተቀላቀለው አማኑኤል በግሉ ልምምዶችን ሲሰራ ቆይቷል።
አማኑኤል ባሳለፍነው ዓመት የውድድር ዘመን 19ኛ ሳምንት ፤ ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ላይ ጉዳቱን ማስተናገዱ የሚታወስ ነው።
በመቀሌ 70 እንደርታ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ ያሸነፈው አማኑኤል ፋሲል ከነማን ከተቀላቀለ በኋላ በ14 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 962 ደቂቃዎች በመጫወት 4 ግቦችን ከመረብ አሳርፏል።
- ማሰታውቂያ -
አማኑኤል ምናልባት በ5ኛው ሳምንት ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በሚገጥምበት አልያም በ6ኛው ሳምንት አርባምንጭ ከተማን በሚገጥምበት ጨዋታ ዳግም በሜዳ ላይ እንደምናየው ይጠበቃል።