የ2016 ዓ.ም የውድድር ዘመን የከፍተኛ ሊግ ተሳታፊ የሆነው አርባምንጭ ከተማ እግርኳስ ክለብ ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ክለቡን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት እየመራ የቆየዉን በረከት ደሙን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል።
የክለቡ የስራ አመራር ቦርድ ክለቡን በጊዜያዊነት እየመሩ የቆዩትን አሰልጣኝ በረከት ደሙን በሁለት አመት ኮንትራት የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው ሾመዋል።
አሰልጣኙ ምክትል አሰልጣኞችን የመሰየም እና ክለቡን በአጭር ጊዜ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የመመለስ ሀላፊነት እንደተጣለባቸዉ ለማወቅ ችለናል።