አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የሶስት ነባር ወሳኝ ተጨዋቾችን ውል አራዘመ
በወጣቱ ዋና አሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመራው በ2016 ዓ/ም የከፍተኛ ሊጉ የአሸናፊዎች አሸናፊ ክለብ አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉም ጥንካሬውን ለማስቀጠል የክለቡ ነባር ተጨዋቾችን ውል የማደስ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል ።
በዚህም በከፍተኛ ሊጉ ክለቡን በትጋት ያገለገሉና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ያሳደጉ ልጆች ውላቸውን እያደሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል በዛሬው ዕለት ፦
1. አሸናፊ ተገኝ ፦ የመሰመር አጥቂ ስፍራ ተጨዋች
2. ሰራዊት ሰያ ፦ ግብ ጠባቂ
3. አላዛር መምህሩ ፦የመሰመር አጥቂ ስፍራ ተጨዋች ውላቸውን አራዘመዋል።