አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ የኮከቡን ውል አራዝሟል
በወጣቱ ዋና አሰልጣኝ በረከት ደሙ የሚመራው በ2016 ዓ/ም የከፍተኛ ሊጉ የአሸናፊዎች አሸናፊ ክለብ አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉም ጥንካሬውን ለማስቀጠል የክለቡ ነባር ተጨዋቾችን ውል የማደስ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል ።
ክለቡ በ2016 ዓ/ም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ኮከብ ተጨዋች የክለቡን የመሃል ሜዳ ሞተሩን እንዳልካቸው መስፍንን በዛሬው ዕለት ውሉን አራዝሟል ።