አዞዎቹ ከፍተኛ ተስፋ የተጣለበትን ወጣት የግራ ተከላካይ ካለብ በየነ ከሀዲያ ሆሳዕና 3ኛ ፈራሚ አድርጓል ።
አርባምንጭ ከተማ ሶስተኛውን አዲስ የክለቡን ፈራሚ ከሀዲያ ሆሳዕና በዛሬው ዕለት አስፈርሟል።
አርባምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በፕሪሚየር ሊጉም ጥንካሬውን ለማስቀጠል የክለቡ ነባር ተጨዋቾችን ውል የማደስና አዳዲስ ተጨዋቾችን ወደክለቡ የማቀላቀል ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል።
ክለባችን በዚህም በዛሬው ዕለት ከታዳጊ ጀምሮ በሀዲያ ቤት ድንቅ ብቃት በማሳየት ላለፉት 4 ዓመታት የቆየውን ተስፈኛ ወጣቱን ካለብ በየነን የግሉ አድርጓል።