ከተጀመረ 50ኛ አመቱን የደፈነው እና ከዚህ ቀደም ለ43 ያህል ጊዜያት የተደረገው የአለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ለ44ኛ ጊዜ ነገ ጠዋት ላይ በአውስትራሊያ ባትረስት ከተማ ይደረጋል ።
ኢትዮጵያ በዓለም ሀገር አቋራጭ ውድድር በርካታ ሜዳልያዎችን መሰብሰብ ከቻሉ ሀገራት ከቀዳሚዎቹ ተርታ የምትቀመጥ ናት ።
በዘንድሮው ውድድርም ኢትዮጵያ በአምስት የወድድር ዘርፎች ትሳተፋለች ።
በሴቶች 6 ኪ.ሜ ፣ በሴቶች 8 ኪ.ሜ ፣ በወንዶች 8 ኪ.ሜ ፣ በወንዶች 10 ኪ.ሜ እንዲሁም በድብልቅ ሪሌይ ውድድሮቹ ይደረጋሉ ።
- ማሰታውቂያ -
በመድረኩ ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ሱሉልታ ላይ በተደረገው 40ኛው የኢትዮጵያ ሀገርአቋራጭ ውድድር ላይ ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ መውጣት የቻሉ ናቸው ።
በእያንዳንዱ ውድድር ላይ ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶች ዝርዝር ይህን ይመስላል ።
በወንዶች 10 ኪ.ሜ
ሰለሞን ባረጋ
በሪሁ አረጋዊ
ሀይለማርያም አማረ
ጌታነህ ሞላ
ሞገስ ጥዑማይ
ጪምዴሳ ደበሌ
በሴቶች 10 ኪ.ሜ
ለተሰንበት ግደይ
ሀዊ ፈይሳ
ፅጌ ገብረሰላማ
ውዴ ከፋለ
ፎተይን ተስፋዬ
ጌጤ አለማየሁ
ከ20 ዓመት በታች ወንዶች 8 ኪ.ሜ
አቤል በቀለ
ይስማው ድሉ
ቦኪ ድሪባ
በረከት ነጋ
በረከት ዘለቀ
ኩማ ግርማ
ከ20 ዓመት በታች ሴቶች 6 ኪ.ሜ
ትነበብ አስረስ
መዲና ኢሳ
ሰናይት ጌታቸው
ለምለም ንብረት
መልክናት ውዱ
መሰረት የሻነህ
ድብልቅ ሪሌይ 8 ኪ.ሜ
ጌትነት ዋለ
ሀየሎም ብርቄ
መቅደስ አበበ
አደምና ካሳዬ
የውድድር ሰዓቶች
1:30 ድብልቅ ሪሌይ 8 ኪ.ሜ
2:10 የሴቶች ከ20 ዓመት በታች 6 ኪ.ሜ
2:50 የወንዶች ከ20 ዓመት በታች 8ኪ.ሜ
3:30 የአዋቂ ወንዶች 10 ኪ.ሜ
4:30 የአዋቂ ሴቶች 10 ኪ.ሜ