” ስለ እርቁ የሰማሁት ነገር የለም”
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ
” አባገዳዎቹ በሰጡኝ ቀጠሮ ለዕርቁ ቦታው ተገኝቻለሁ”
አትሌት ገዛኸኝ አበራ
ከፓሪስ ኦሎምፒክ ምርጫና ጉዞ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ አለመግባባት ውስጥ የገቡትን የአትሌቲክስ ስፖርት ወዳጃሞች ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና አትሌት ገዛኧኝ አበራን ለማስታረቅ የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል።
- ማሰታውቂያ -
በሃይሌ ግራንድ ሞል ሊካሄድ ታስቦ በነቀረው እርቅ ጀግናው አትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ፣ የቴኒስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ታምራት በቀለና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ከአባገዳዎች ጋር በመሆን ሽምግልና ሊቀመጡ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያስረዳል።
በፓሪስ በድብቅ የተቀዳውና መላው ህብረተሰብ የሰማው ድምጽ ተወዳጇ የአትሌቲክስ ሰው ደራርቱ ቱሉ ያልተጠበቀ ድምጽ ከተሰማ በኋላ የተፈጠረው ቅሬታ ደግሞ ልዩነቱን እንዳሰፋው ይታወሳል ። ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በጨዋታ መልክ የተነሳ መሆኑን ገልጻ ገዛኦኝና ቤተሰቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ ብላ ልዩነቱን ለማብረድ ሞክራ የነበረ ቢሆንም እስከዛሬ ድረስ ገዛኧኝና ባለቤቱ እልፎፍነሽ ጋር አለመሄዷ ታውቋል።
አባገዳዎች በኢትዮጵያ ባህል ትልቅ እሴት በሆነው ሽምግልና ለማስታረቅ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል። በጉዳዩ ዙሪያ የተጠየቀው አትሌት ገዛኧኝ አበራ ለሀትሪክ ድረገጽ እንደተናገረው “ለአባገዳዎች የሽምግልና ጥሪ ትልቅ ክብር አለኝ እርቁኝን ተቀብዬ ቦታው ተገኝቻሐሁ የማውቀው ይሄንን ነው በኔ በኩል ዕርቁ መቅረቱ ለምን እንደሆነ አልገባኝም ምክንያቱን በቀጣይ የማጣራ ይሆናል” ሲል ተናግሮል። ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ በስልክ ለሀትሪክ ድረ ገጽ እንደገለጸችው “ስለተባለው ዕርቅ የማውቀው ነገር የለም አሁን በሌላ ስራ ላይ ተወጥሬ እገኛለሁ በቀጣይ ግን ዕርቁ የሚቀር አይመስለኝም ” ስትል ምላሿን ሰጥታለች።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋናና ም/ል ፕሬዝዳንት የሆኑት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና አትሌት ገዛኧኝ አበራ መሃል ልዩነቱ አለመወገዱ ለቀጣይ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉዞ ላይ ሌላ ልዩነት እንዳይፈጥር ተሰግቷል። የሁለቱ ወገኖች እርቅና የስፖርቱ ሰላም እንዲጠበቅ በመንግስት በኩልም ድጋፍ ቢኖረውም አለመሳካቱ ሌላ የማይታይ የግለሰቦች ስውር እጅ ይኖር ይሆን እንዴ አስብሏል።