ከሁለት ሳምንታት በፊት ከአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ጋር ለቀጣዮቹ ሁለት አመታት አብሮ ለመስራት በቃል ደረጃ የተስማሙት የጣና ሞገዶቹ በዛሬው ዕለት ደግሞ ገርጅ አካባቢ በሚገኘዉ ኔክሰስ ሆቴል በይፋ ከአሰልጣኙ ጋር ተፈራርመዋል።
በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ እየተመሩ የዉድድር አመቱን የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሰባተኝነት ደረጃ ያገባደዱት የጣና ሞገዶቹ ዉድድር አመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በስምምነት ከአሰልጣኛቸዉ ጋር መለያየታቸው ይታወሳል።
ከአሰልጣኛቸዉ ጋር ከተለያዩ በኋላ አዲስ አሰልጣኝ ለመሾም በዝግጅት ላይ የነበሩት ባህርዳር ከተማዎች በመጨረሻም ዕቅዳቸዉ ሰምሮ የቀድሞዉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም የዉድድር አመቱን በሰበታ ከተማ ያሳለፉትን አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከሁለት ሳምንታት በፊት መሾማቸው ይታወቃል።
- ማሰታውቂያ -
ከ2004–2009 የየመንን ከ23 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን፤
ከ2009–2010 የየመንን ዋናው ብሄራዊ ቡደን፤
ከ2010- 2012 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን፤
ከ2013–2014 ሰበታ እግር ኳስ ክለብን ማሰልጠን የቻሉት አሰልጣኙ አሁን ደግሞ በሁለት አመት የዉል ስምምነት ወደ ባህርዳር ከተማ አምርተዋል።
ኢንስትራክትር አብርሃም መብራቱ የየመን በሄራዊ ቡደንን ይዘው ለመጀመርያ ጊዜ ለኢስያ ካፕ ማለፋቸው ይበልጥ በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ዕዉቅና እንዲያገኙ አድርጓቸዋል። ከ22 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኑን ይዘው የተለያዩ የማጣርያ ጨዋታዎችን ማድረግ የቻሉት አሰልጣኙ በኋላም የስፖርት ፌደሬሽኑ ቴክኒካል ዳይሪክተር በመሆንም ማገልገል ችለዋል። በ2009 አመት ዋናዉን የየመን ብሔራዊ ቡድኑን በመያዝ የውስጥ ውድድር ባልነበረበት ሁኔታ ለኢስያ ካፕ ለመጀመርያ ጊዜ በማሳለፍ ታሪክ ተሰርተዋል። ከዚያም በመቀጠል የሀገሩን ጥሪ ተቀብሎ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ዋልያዎቹን ማሰልጠን ችለዋል።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቆይታቸውም እጅግ ስኬታማ የነበሩት አሰልጣኙ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ውድድር ብሄራዊ ቡደኑ እንዲያልፍ ጉልህ ድርሻን መወጣታቸው ይታወሳል። ከብሄራዊ ቡድኑ ባልተጠበቀ ሁኔታ የተለያዩት ኢንስትራክተር አብርሃም በመቀጠልም ወደ ሰበታ ከተማ በማምራት የአንድ አመት ቆይታ ማድረግ ችለዉ ነበር። በመጨረሻም አሰልጣኙ ለሁለት አመታት በባህርዳር ከተማ ቤት ለመቆየት ፊርማቸዉን ዛሬ በይፋ አኑረዋል።
ከፊርማ ስነስርዓቱ በኋላም አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ በስፍራው ለነበሩ አካላት የሚከተሉትን ሀሳቦች አካፍለዋል።
”ከባሕር ዳር ጋር እንድፈርም ብዙ ምክንያቶች አሉኝ:-
1-የክለቡ አደረጃጀት ዘመናዊ ለመሆን የተዘጋጀ እና የሚመች ስለሆነ።
2-የከተማው አመራሮች እና ባለሀብቶች ከክለቡ ጋር ለመስራት ዝግጁወች መሆናቸው።
3-ባሕር ዳር ብዙ አቅም ያላት እና ብዙ ተጫዋቾች መውጣት የሚችሉበት ከተማ ስለሆነች ። እናም ታዳጊወች ላይ ለመስራት የተመቸች ከተማ በመሆኗ ምክንያት ምርጫቸዉ እንዳደረጓት ተናግረዋል።
በተጨማሪም በባሕር ዳር ከተማ ቤት በሁለት ዓመት ውስጥ ጠንካራ እና ተፎካካሪ ክለብ ለመስራት እናስባለን” ሲሉ ሀሳባቸውን ቋጭተዋል።
በተጨማሪም በባሕር ዳር ከነማ ቤት ብዙ አዳዲስ ነገሮችን ለመጀመር ማቀዳቸዉንም የክለቡ የበላይ አካላት ገለፃ አድርገዋል። ለአብነትም:-
1- ሌጀንድ የሆኑ ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ በስካውቲንግ እና በመሳሰሉ የመማሪያ መንገዶች ክለቡን ይቀላቀላሉ በስታስቲክስም ጨምሮ፤ አዳነ ግርማም አንዱ ሊሆን እንደሚችል ንግግር ላይ ነን በአብዛኛው ክልሉ ላይ ያሉ ሌጀንድ ተጫዋቾች ላይ አተኩረን ለአሰልጣኝነት እናበቃለን።
2- ክለቡ የምግብ እና የሳይኮሎጅ ባለሙያ በአሰልጣኝ ቡድኑ ውስጥ ያካትታል ።
3- ክለቡን እጅግ ወደ ዘመናዊ መንገድ ለማስጓዝ አስፈላጊ የሆኑ ስራወችን ሁሉ ለመስራት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል።