ባህርዳር ከነማዎች ከሊጉ መሪ ጋር ያላቸዉ የነጥብ ልዩነት የሰፋበት እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕናዎች ደረጃቸዉን ከፍ ያደረጉበት ጨዋታ በከቤራዎቹ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
የጨዋታዉ የመጀመሪያ ክፍለ ግዜ ፈጣን በሆነ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ገና ከጅምሩ የባህርዳር ከነማዎቹ አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ ያገኛት ኳስ በሀዲያ ሆሳዕናዎቹ በረኛ የተመለሰበት ወደ ጎል የመታት ኳስ ተጠቃሽ ናት።
የባህር ዳሮቹ ፉዓድ ፈረጃ በ6ኛዉ ደቂቃ ላይ ጉዳት አስተናግዶ በቻርልስ ሪቫኑ ተቀይሮ ከወጣ በኋላ የጨዋታ ብልጫዉ ወደ ሀዲያ ሆሳዕናዎች ያመራ ሲሆን ሠመረ ሀፍታይ በ29ኛዉ ደቂቃ ለሀዲያ ሆሳዕናዎች ኳሱን ከመረቡ አገናኝቶ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕና 1-0 በሆነ መሪነት ቀጥሎ የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
- ማሰታውቂያ -
ጨዋታው ከእረፍት መልስ በ1-0 ዉጤት ለአምስት ደቂቃዎች ብቻ የቀጠለ ሲሆን ተመስገን ብርሀኑ ለሀዲያ ሆሳዕናዎች ኳሱን ከመረብ አገናኝቶ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕናዎች 2-0 መሪነት የቀጠለ ቢሆንም 67ኛው ደቂቃ ላይ ቻርለስ ሪቫኑ ለባህርዳሮች ኳሱን ከመረብ አገናኝተ ጨዋታዉ ወደ 2-1 አምርቷል።
ባህርዳሮች ከግቧ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ጎል ለመድገም ተጭነዉ መጫወትን ቀጥለዉ በተደጋጋሚ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና የግብ ክልል ማምራት የቻሉ ሲሆን በጨዋታዉ መገባደጃ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ላይ በዱሬሳ ሹቢሳ በኩል ለጎል የቀረበ ኳስ አግኝተዉ የነበረ ቢሆንም ሳይጠቀሙበት ቀርተዉ ጨዋታዉ በሀዲያ ሆሳዕና 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት ባህርዳር ከነማ ከመሪዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ያለዉ የነጥብ ልዩነት ወደ 5 አድጓል።