አሰልጣኝ አብርሀም መብራቱን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደስብስባቸዉ በመቀላቀል ዝግጅታቸውን በከማቸዉ ባህርዳር ከተማ ሲያደርጉ የቆዩት የጣና ሞገዶቹ በዛሬዉ ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በምድብ ሁለት ከአዳማ ከተማ ጋር ጨዋታቸዉን ከማድረጋቸው በፊት ቡድኑን በአምበልነት የሚመሩትን ተጫዋቾች አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ አሳዉቀዋል።
ላለፉት ዓመታት የቡድኑ ዋና አንበል የነበረው ደረጀ መንግስቱ ወደ የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱን በመቀላቀሉ ምክንያት የቡድን አንበላቸውን የቀየሩት አሰልጣኙ በዋና አንበልነት ፍቅረ ሚካኤል አለሙን ያደረጉ ሲሆን ሁለተኛ አንበል በማድረግ ደግሞ ከኢትዮጵያ ቡና ባሳለፍነው ዓመት ክለቡን የተቀላቀለውን የመስመር ተጫዋች አህመድ ረሽድ (ሽሪላው) በማድረግ ሾመዋል።