በተጠናቀቀዉ የዉድድር አመት በአሰልጣኝ አብርሐም መብራቱ እየተመሩ የተጠበቁን ያህል ዉጤታማ መሆን ያልቻሉት የጣና ሞገዶቹ በቀጣይ አመት በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነዉ ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ በዝዉዉር መስኮቱ በሰፊዉ በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ ይታወቃል። በዚህም ሰሞኑን ከክለቡ ሰዎች ጋር ንግግር ሲያደርግ የነበረዉ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ያሬድ ባየህ በዛሬዉ ዕለት ወደ ባህርዳር ከተማ ማምራቱ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደም ለአማራ ዉሀ ስራ እና ዳሽን ቢራ እንዲሁም ያለፉትን አራት አመታት ለአፄዎቹ መጫወት የቻለዉ ተከላካዩ ያሬድ ባየ ረዘም ላሉ አመታት ከቆየበት ፋሲል ከነማ ጋር በመለያየት ቀጣዮቹን ሁለት አመታት ለጣና ሞገዶቹ ለመጫወት ፊርማውን አኑሯል።