የዉድድር አመቱን ከፈረሰኞቹ ጋር ሻምፒዮን መሆን የቻለዉ እና በርከት ላሉ አመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት መጫወት የቻለዉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ የአብስራ ተስፋየ ወደ ባህርዳር ከተማ ማምራቱ ተረጋግጧል።
ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ዉሉን ያራዝማል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረዉ ተጫዋቹ ከክለቡ ጋር ከስምምነት ላይ መድረስ ባለመቻላቸዉ ምክንያት ሁለት አመት በሚቆይ የስምምነት ዉል ለጣና ሞገዶቹ ለመጫወት ፊርማዉን አኑሯል።