የዉድድር አመቱን ከጅማ አባጅፋር ጋር ያሳለፈው ወጣቱ ግብ ጠባቂ የጣና ሞገዶቹን መቀላቀሉ እርግጥ ሆኖአል።
አሠልጣኝ አብርሃም መብራቱን በዋና አሰልጣኝነት ከሾሙ በኋላ በንቃት በዝዉዉሩ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት የጣና ሞገዶቹ አሁን ደግሞ ወጣቱን ግብ ጠባቂ አቡበከር ኑሪን ማስፈረማቸዉ ታዉቋል።
በጅማ አባ ጅፋር ቤት የውድድር ዓመቱን ያሳለፈዉ ተስፈኛው ግብ ጠባቂ አቡበከር ምንም እንኳን ዘንድሮ በኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ላይ ክለቡ ጅማ ውጤታማ ዓመትን ማሳለፍ ባይችልም በግሉ እጅግ አስገራሚ ብቃቱን በማሳየት አመቱን ማጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህ ብቻ ሳይሆን ቡድኑ ጅማ አባጅፋር ከሊጉ መዉረዱን ተከትሎ የትግራይ ክልል ክለቦችን ተክቶ ዳግም በሊጉ ለመሳተፍ በነበረው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዉድድር ላይ በሚያስደንቅ ብቃት ክለቡ ጅማ ዳግም ወደ ሊጉ እንዲመለስ የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱ ይታወሳል።