አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱን ከሾሙ በኋላ በዝዉዉሩ ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ባህርዳሮች በዛሬው ዕለት ደግሞ በሴካፋ የእስካሁን ዉድድር ላይ ማንፀባረቅ የቻለዉን አሊ ሱለይማን ማስፈረማቸዉ ታዉቋል።
በሴካፋ ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ 3ለ3 በሆነ የአቻ ውጤት ነጥብ በተጋሩበት ጨዋታ ለሀገሩ ኤርትራ ሶስት ጎል በማስቆጠር “ሀትሪክ” የሰራው አሊ ሱሌይማን ከደቂቃወች በፊት ለባህር ዳር ከነማ ለመጫወት ስምምነት ላይ መድረሱን ክለቡ ይፋ አድርጓል።
ዝዉዉሩን ተከትሎ በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ላይ የሚጫወት ሁለተኛው ኢርትራዊ ተጫዋች ለመሆን ችሏል።