በአሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ እየተመሩ በዝዉዉር ገበያዉ ላይ በንቃት በመሳተፍ ላይ የሚገኙት ባህርዳር ከተማዎች አሁን ደግሞ የዉድድር አመቱን ከሰበታ ከተማ ጋር ያሳለፈዉን ጋናዊ የመስመር አጥቂ ኦሴ ማዉሊ የግላቸዉ ማድረግ ችለዋል።
ከዚህ በፊት በፋሲል ከነማ ቤት እና በመቀለ 70 እንደርታ ተጫዉቶ ማሳለፍ የቻለዉ ተጫዋቹ አሁን ደግሞ የቀድሞዉ አሰልጣኙን አብርሃም መብራቱን በመከተል ባህርዳር ከተማን መቀላቀሉ ተረጋግጧል።