ከሰአታት በፊት ባህርዳር ከተማዎች ከአጥቂዉ ወሰኑ አሊ እና ከቀኝ መስመር ተከላካዩ ሚኪያስ ግርማ ጋር በስምምነት መለያየታቸዉን መዘገባችን ይታወሳል። አሁን ደግሞ ከሌላኛዉ ተጫዋቻቸዉ ሳምሶን ጥላሁን ጋር መለያየታቸዉ ታዉቋል።
የቀድሞዉ የደደቢት እና ኢትዮጵያ ቡና ተጫዋች የነበረዉ ሳምሶን ጥላሁን ያለፉትን ሁለት የዉድድር አመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ካሳለፈ በኋላ ምንም እንኳን ቀሪ የአንድ አመት ዉል ቢኖረዉም በስምምነት ከክለቡ ጋር መለያየቱ ተረጋግጧል።
በተያያዘም ተጫዋቹ እንደ ክለብ አጋሮቹ ወሰኑ አሊ እና ሚኪያስ ግርማ ሁሉ በቀጣይ ወደ ሌላ ክለብ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።