የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን CAF በ2024 የአፍሪካ ዋንጫን ለመምራት የዝግጅት ኮርስ የሚወስዱ የ69 ዳኞችን ዝርዝር ይፋ አድርጎል ።
በዝርዝሩ ከተካተቱ ዳኞች መካከልም 32ቱ ዋና ዳኞች ሲሆኑ ኢንተርናሽናል አርቢትር ባምላክ ተሰማም ስሙ ተካቷል ።
ካፍ ይፋ ባደረገው ዝርዝር ከ15 ሀገራት የተወጣጡ 69 ዳኞት የተመረጡ ሲሆን ግብፅ እና አልጄሪያ ሶስት ሶስት ዳኞች በማስመረጥ በቀዳሚነት ተቀምጠዋል ።
የተመረጡት ደኞችም በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ የተለያዩ መመዘኛዎችን ወስደው የመጨረሻ ውድድሩን የሚመሩ ዳኞች ይፋ ይደረጋሉ ።