በቶኪዮ ኦሎምፒክ በ እግር ኳስ ዳኝነት ኢትዮጵያን የወከለው ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በ ኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ፣ በ ኢ.እ.ፌ የ ብሔራዊ ዳኞች ምክትል ሰብሳቢ አቶ ልኡልሰገድ በጋሻው፣ በኢ.እ.ፌ ዋና ጸሀፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን እና በሙያ አጋሮቹ አቀባበል ተደረገለት።
ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ ” የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ የ ብሔራዊ ዳኞች ም/ሰብሳቢ እና ፌዴሬሽኑ ዋና ጸሀፊ ከ ሙያ አጋሮቼ ጋር በመሆን በ ቶኪዮ ለ ነበረኝ ቆይታ እንደ ታላቅ አትሌቶቻችን ኤርፖርት ድረስ መጥተው ስለተቀበሉኝ ከፍተኛ ደስታ እና ኩራት ተሰምቶኛል ።
- ማሰታውቂያ -
ይህ ለማንኛውም ስፖርተኛ ፣ ሀገርን ለሚወክል ሁሉ ያለን ትልቅ አክብሮት ያሳያል፣ ስለሁሉም አመሰግናለሁ። “
” ኮረተንብኃል ይህ ለሌሎች ሙያተኞችም ትልቅ መነሳሳትን ያመጣል እና በርታ ፣ የእርሱ እዚህ ቦታ መገኘት የጠንካራ ስራ ውጤት ነው እና ሁሉም በያለበት ጠንክሮ እንዲሰራ አሳስባለሁ ” ሲሉ የኢ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናግረዋል ።
Via- ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን