ኢትዮጵያዊው አለም አቀፍ አልቢተር ባምላክ ተሰማ ወይሳ ወደ ግብፅ ካይሮ ቀጣዩን ስድስት ቀናት ቆይታውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል ።
አልቢተር ባምላክ ተሰማ ካፍ ከ ጥቅምት አንድ እስከ አምስት ባዘጋጀው የካፍ የዳኞች ስልጠናን ለመካፈል ስም ዝርዝራቸው ከተካተተ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ አልቢተር ውስጥ ነው ።
በካፍ በተዘጋጀው በዚህ ስልጠና ላይ ሰላሳ ሶስት ዳኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ሲጠበቅ ስልጠናው ከነገ አንስቶ እስከ ፊታችን ሐሙስ ድረስ እንደሚካሄድ የወጣው መርሐ ግብር ያሳያል ።