የኢትዮጵያ እግር ኳስ ተጫዋቾች ማህበር የ2016 ዓመተ ምህረት የዓመቱ ኮከቦችን በሶስት ዘርፎች ይፋ አድርጓል።
ማህበሩ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ባሲሩ ዑመር የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች እንዲሁም የቡድን አጋሩ ፍሬው ጌታሁን የዓመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመሆን ተመርጠዋል።
በተጨማሪም የአዳማ ከተማው ቢንያም አይተን የዓመቱ ወጣት ኮከብ ተጫዋች በመሆን ተመርጧል።
የኮከቦቹ ምርጫ ከአስራ ስድስቱ የውድድር ዓመቱ የሊጉ ተሳታፊ ክለብ አምበሎች በተሰበሰበ ድምፅ ነው።