የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች።
በሳምንቱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ማክሰኞ ጥር 30 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በተጫዋቾች ደረጃ ሐቢብ ከማል (አርባምንጭ ከተማ) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ወስኗል።
በክለብ ደረጃ አርባምንጭ ከተማ ክለቡ ከ ሲዳማ ቡና ጋር ባደረገው የ11 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ አምስት ተጫዋቾች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
- ማሰታውቂያ -
በተጨማሪም በደጋፊዎች አስነዋሪ ድርጊት ሀዲያ ሆሳዕና ክለቡ ከ ጅማ አባ ጅፋር ጋር በነበረው የ11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ስለቀረበበት ፥ በተጨማሪም ወላይታ ድቻ ክለቡ ከ አዲስ አበባ ከተማ ጋር በነበረው የ 11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ተመሳሳይ ሪፖርት ስለቀረበበት የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋትና ከዚህ በፊት የተሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ታሳቢ በማድረግ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር 750000/ መሰረት ሁለቱም ክለቦች ሰባ አምስት ሺህ/ እንዲከፍሉ ተወስኗል።
በተያያዘም ድሬደዋ ከተማ ክለቡ ከ ሃዋሳ ከተማ ጋር በነበረው የ11ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል። የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ከለቡ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 4(ሀ) ብር 50000/ሃምሳ ሺህ/ እንዲከፍል ተወስኗል።
በመጨረሻም የኮቪድ የምርመራ ውጤት:- በአንድ ማዕከል የኮቪድ ምርመራ ለተጫዋቾች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ዳኞች ተደርጎ። ከአጠቃላይ 576 ምርመራ አንድም ፓዘቲቨ የተገኘ ውጤት የለም።