የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ አርብ ሰኔ 10 2014 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ የዲሲፕሊን ውሳኔዎችን አሳልፏል።
በተጫዋቾች ያኩቡ መሀመድ (ሲዳማ ቡና) ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ 1 ጨዋታ እንዲታገድ ፥ ላርዬ ኢማኑኤል(መከላከያ) ፣ አዮብ ዓለማየሁ(ጅማ አባ ጅፋር) ፣ ቶማስ ስምረቱ(አዳማ ከተማ) በተለያዩ 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክተዋል በመሆኑም ተጫዋቾቹ ለፈፀሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገዱና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 /አንድ ሺ አምስት መቶ/ እንዲከፍሉ ሲወሰን ኢዮብ ዓለማየሁ (ጅማ አባ ጅፋር ) ክለቡ ከ ሀዲያ ሆሳዕናጋር ባደረገው የ 26 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ ላይ በ21ኛው ደቂቃ ላይ ከዳኛ እይታ ውጭ የተጋጣሚ ተጫዋችን በቁጣ አድራጎት በመራገጡ ከሜዳ መወገድ እንደነበረበት በዕለቱ የጨዋታ ታዛቢ ሪፖርት ቀርቦበት ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መሰረት 4 ጨዋታ እንዲታገድ ና በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 3000 /ሶስት ሺ/ እንዲከፍል ወስኗል።
በመጨረሻም ለአቶ እሱባለው (ባህርዳር ከተማ-የቦርድ አባል) ፣ ለሲዳማ ቡና እግር ኳስ ቡድን መሪ እና ለአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ወጌሻ አደም መሀመድን ለማነጋገር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ጥሪ አድርጓል።