የ2015 ዓ.ም የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር የመጀመሪያ ዙር ባሳለፍነው ረቡዕ ተጠናቆ የሁለተኛ ዙር አንድ ጨዋታም በዕለተ ሀሙስ ተካሂዷል ።
ውድድሩ መስከረም 20 በባህርዳር ዓለም ዓቀፍ ስታድየም በወልቂጤ ከተማ እና አርባምንጭ ከተማ መካከል በተደረገ ጨዋታ ጅማሮውን አድርጓል ። እስከ አምስተኛ ሳምንት ድረስ ያሉ ጨዋታዎች በባህርዳር ከተማ ከተደረጉ በኋላ ከስድስተኛ ሳምንት ጀምሮ በድሬደዋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።
በዚህ ዘገባችን በመጀመሪያው ዘር የተመዘገቡ የተለያዩ ቁጥራዊ መረጃዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል ።
በመጀመሪያው ዙር 120 ጨዋታዎች ሲደረጉ 295 ግቦች ከመረብ አርፈዋል ። ከነዚህ ጨዋታዎች መካከልም 79 ጨዋታዎች በመሸናነፍ ሲጠናቀቁ 41 ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ፍፃሜያቸውን አግኝተዋል ።
- ማሰታውቂያ -
ባለሜዳ ሆነው ጨዋታውን የሚያካሂዱ ክለቦች የማሸነፍ ንፃሬያቸው 27.5%(33/120) ሲሆን የእንግዳ ክለቦች ደግሞ 38.33%(46/120) ነው ።
– በርካታ ነጥቦችን የሰበሰበው
ቅዱስ ጊዮርጊስ – 32
– ጥቂት ነጥቦችን የሰበሰበው
ለገጣፎ ለገዳዲ – 6
– በርካታ ጨዋታዎችን ያሸነፈው
ቅዱስ ጊዮርጊስ – 9
ኢትዮጵያ መድኅን – 9
– በርካታ ጨዋታዎች ላይ አቻ የተለያየው
አርባምንጭ ከተማ – 8
– በርካታ ጨዋታዎችን የተሸነፈው
ለገጣፎ ለገዳዲ – 11
– ጥቂት ጨዋታዎችን ያሸነፈው
ለገጣፎ ለገዳዲ – 1
ኢትዮ ኤሌክትሪክ – 1
– ጥቂት ጨዋታዎች አቻ የተለያየው
ኢትዮጵያ መድኅን – 3
አዳማ ከተማ – 3
ለገጣፎ ለገዳዲ – 3
– ጥቂት ጨዋታዎች የተሸነፈው
ቅዱስ ጊዮርጊስ – 1
– አራት ክለቦች(ፋሲል ከነማ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ወላይታ ድቻ) በተመሳሳይ 5 ጨዋታዎች አሸንፈው ፣ 6 ጨዋታዎች አቻ ሲለያዩ በ4 ተሸንፈዋል ።
– ሶስት ክለቦች(ኢትዮጵያ ቡና ፣ ወልቂጤ ከተማ እና መቻል)በተመሳሳይ 5 ድል ፣ 5 አቻ እንዲሁም 5 ሽንፈት አስተናግደዋል ።
– በሊጉ 4ኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው ፋሲል ከነማ እና 14ኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው ድሬዳዋ ከተማ መካከል ያለው የነጥብ ልዩነት 4 ብቻ ነው ።
በሊጉ የ15 ሳምንታት ቆይታ 295 ግቦች ተቆጥረዋል ። ይህም ማለት በአማካይ በአንድ ጨዋታ 2.46 ግቦች ይቆጠራሉ ።
በነዚህ 120 ጨዋታዎች 15 አይነት ውጤቶች ተመዝግበዋል ። ከነዚህም መካከል ቅዱስ ጊዮርጊስ ኢትዮጵያ መድኅንን 7 ለ 1 ያሸነፈበት ጨዋታ በሰፊ ውጤት የተጠናቀቀ እና በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል ።
በመጀመሪያው ዙር በቁጥር በርከት ብሎ የተመዘገበው የ1 ለ 0 ውጤት ሲሆን 21 ጨዋታዎች በዚህ ውጤት ተጠናቀዋል ።
– በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ሳምንት
1ኛ እና 8ኛ ሳምንታት – 23
– ጥቂት ግቦች የተቆጠሩበት ሳምንት
12ኛ ሳምንት – 8
– በርካታ ግቦችን ያስቆጠረ ክለብ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – 32
– በርካታ ግቦች የተቆጠሩበት ክለብ
ለገጣፎ ለገዳዲ – 37
– ጥቂት ግብ ያስተናገደው ክለብ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – 9
ሀድያ ሆሳዕና – 9
– በርካታ የፍፁም ቅጣት ምት ያገኘ ክለብ
ወልቂጤ ከተማ – 5
– በርካታ የፍፁም ቅጣት የተሰጠበት ክለብ
አዳማ ከተማ – 2
– በርካታ የፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ክለብ
ወልቂጤ ከተማ – 5
– በርካታ የፍፁም ቅጣት ምት ያመከነ ክለብ
ኢትዮጵያ ቡና – 2
ሀድያ ሆሳዕና – 2
በመጀመሪያው ዙር 540 የቢጫ ካርዶችን 275 የቡድን አባላት (ተጫዋቾች እና የስታፍ አባላት)ተመልክተዋል ። ከነዚህ ካርዶች መካከል 515 ተጫዋቾች ሲሆኑ 25 ደግሞ ሌሎች የቡድን አባላት የመለከቱት ነው ።
23 የቡድን አባላት የቀይ ካርድ ሰለባ ሲሆኑ 16 በሁለተኛ ቢጫ 7 ደግሞ በቀጥታ የቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበቱ ናቸው ።