በግብፅ አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ እየተደረገ በሚገኘዉ የአፍሪካ የሴቶች ቻምፒዩንስ ሊግ የመጀመሪያውን ፍፃሜ ጨዋታ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ እንደምትመራዉ ተረጋግጧል።
በየዞናቸው በነበሩ ዉድድሮች ላይ ቀዳሚቁን ስፍራ ይዘዉ ያጠናቀቁት ስምንት ክለቦች በሚሳተፉበት በዚህ ዉድድር ላይ ዳኛዋ ከዚህ ቀደም ሁለት(1በዋና ዳኝነት 1በአራተኛ ዳኝነት) ያህል ጨዋታዎችን መምራቷ ይታወሳል።
እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፉክክር በነበረበት በዚህ ምርጫ የብቃት ጣሪያዋ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያዊቷ ሊዲያ ታፈሰ በነገዉ ዕለት በጋናዉ ሀሳካስ ሌዲስ እና በደቡብ አፍሪካዉ ማሚሎዲ ሰንዳዉስ መካከል የሚደረገዉን ነፍፃሜ ጨዋታ ከግብፅ ፣ ሞሪታኒያ እና ናይጀሪያዉያን ረዳቶቿ ጋር በመሆን እንደምትመራ ተረጋግጧል።
ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያን በትልልቅ መድረክ እየወከለች ያለችዉ ሊዲያ የፍፃሜዉን ጨዋታ እንድትመራ መመረጧ እጅግ ከፍተኛ ደስታን እንደፈጠረላት እንዲሁም ከሁሉ አስቀድማ ፈጣሪዋን እንደምታመሰግን ገልፃለች።