በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣርያውን እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ በዛሬዉ ዕለት በግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ተጋጣሚዉን ሌዲ ዶቭስን በመለያ ምት አሸንፋል።
ጨዋታዉ ጅማሮ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ አምበል ሎዛ አበራ ክለቧን መሪ ያደረገች ግብ ማስቆጥር የቻለች ቢሆንም ከዕረፍት መልስ ሌዲ ዶቭንሶች ግብ አስቆጥረው አቻ መሆን ችለዋል።
ዘጠናውን ደቂቃ አንድ አቻ በሆነ ዉጤት ያጠናቀቁት ሁለቱ ክለቦች ወደ ጭማሪ 30 ደቂቃ ቢያመሩም ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ በመቅረታቸዉ ወደ መለያ ምት ሊያመሩ ችለዋል።
- ማሰታውቂያ -
ወደ መለያ ምት ያመራዉ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5ለ3 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህ መሰረትም ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች ተጋጣሚያቸዉን ሌዲስ ዶቭ በመለያያ ምት በመርታት ለፍፃሜው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።
በፍፃሜውም የኬንያውን ቪሂጋ ክዊንስን የሚገጥመው ንግድ ባንክ አሸንፎ ዋንጫውን ካነሳ በግብፅ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ ተሳታፊ ይሆናል።