ለ25ኛ ጊዜ እ.አ.አ በ2025 ለሚደረገው እና አዘጋጁ እስካሁን ባልተለየው የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣሪያ የሴካፋ ዞን የምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሆኗል።
በታንዛንያ ዋና ከተማ ዳሬ ሰላም በሚደረገው ውድድር ኢትዮጵያን ጨምሮ ዘጠኝ የዞኑ ሀገራት በማጣሪያ ውድድሩ ለመሳተፍ ማረጋገጫ መስጠታቸውንም ሴካፋ ይፋ አድርጓል።
ዘጠኙ ሀገራት በሁለት ምድቦች ዕጣ የወጣላቸው ሲሆን ኢትዮጵያ አራት ሀገራት በተመደቡበት ምድብ ሁለት ስትደለደል ኡጋንዳ ፣ ደቡብ ሱዳን እና ብሩንዲ በምድቡ የተካተቱ ሀገራት ናቸው።
በምድብ አንድ ደግሞ የአዘጋጁ ሀገር ታንዛኒያ ፣ ሱዳን ፣ ሩዋንዳ ፣ ጅበቲ እና ኬንያ ተደልድለዋል።
- ማሰታውቂያ -
በወድድሩ ለፍፃሜ የሚደርሱት አልያም የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ቡድኖች ዞኑን በመወከል በ20 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ይሳተፋሉ።
በዳሬ ሰላም የሚደረገው ወድድድር ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 10 ድረስ ይደረጋል።
ኢትዮጵያ በዚህ ወድድር ላይ ለሰባት ያህል ጊዜ የተሳተፈች ሲሆን ሁለት ጊዜ የአራተኛ ደረጃን ይዛ ስታጠናቅቅ ሁለት ጊዜ ደግሞ የመጨረሻ አራቱን መቀላቀል(የደረጃ ጨዋታ ባልነበረባቸው ውድድሮች) ችላለች።
ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ የተሳተፈችውም ከ23 አመታት በፊት አዲስ አበባ ላይ በተዘጋጀው ውድድር በድዬጎ ጋርዝያቶ በተመራው ቡድን ነበር።