በዛሬው ዕለት ካፍ መደበኛ ስብስባውን በራባት ሞሮኮ በማካሄድ ላይ ሲገኝ በርካታ ውሳኔዎች እንደሚሰሙ ይጠበቃል ።
አሁን በወጡ መረጃዎች ኢትዮጵያ የሴካፋ ሲኒየር ዋንጫን ለማዘጋጀት ፈቃደኝነቷን መግለጿን ተከትሎ ውድድሩን እንድታዘጋጅ ተመርጣለች ።
የመጪው የሴካፋ ሲንየር ዋንጫ ከ 23 ዓመታ በታች ተጫዋቾች ብቻ እንዲሳተፉበት ሲገለፅ ውድድሩ የሚካሄድበት ቀናት ወደፊት እንደሚገለፅ ይፋ ሆኗል ።
ኢትዮጵያ ውድድሩን ከ ስድስት ዓመታት በፊት ስታስተናግድ በ ሚሉቲን ሰርጆቪች ሚቾ ይሰለጥኑ የነበሩት ዩጋንዳዎች ውድድሩን በበላይነት ማጠናቀቃቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ።