አመታዊው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ /ሲቲ ካፕ/ የፊታችን ጳጉሜ 4/2015 እንዲጀመር የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ወሰነ።
ከፌዴሬሽኑ በተገኘ መረጃ መሰረት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላቱ ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ 17ኛው የከተማው ዋንጫ በዕለተ ቅዳሜ ጳጉሜ አራት እንዲጀመር ወስነዋል። የውድድሩ ቅድመ ዝግጅት አስቀድሞ የተጀመረ ሲሆን ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ውድድሮች የተሻለ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ መሂኑ ተገልጿል።
የዘንድሮው የሲቲ ካፕ ውድድር በስድስት ወይም በስምንት ክለቦች መሃል ይካሄዳል ተብሎም ይጠበቃል።