በቅርቡ ባህርዳር ከተማን ለማሰልጠን የተስማሙት የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ በላይቤሪያ የእግርኳስ አሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ያገኘነዉ መረጃ ይጠቁማል።
የካፍ ኤሊት ኢንስትራክተር አብርሀም መብራቱ በላይቤሪያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋባዥነት ለእግርኳስ አሰልጣኞች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን ፤ ስልጠናው ከኦገስት 18 እስከ 29/2021 የሚቆይ ሲሆን በስልጠናው ከላይቤሪያ የተዉጣጡ አሰልጣኞች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙም ታዉቋል።
ኢንስትራክተሩ ስልጠናውን ካጠናቀቁ በኋላም ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ከባህርዳር ከተማ ጋር የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸዉን እንደሚጀምሩ ይጠበቃል።