ውጤታማ ለመሆንና ተፎካካሪ ቡድን ለመገንባት የተጨዋቾችን ሞራል መገንባትና ፍላጎታቸውን ሟሟላት የግድ ነው ሲል ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ለክለቡ ባስገባው ደብዳቤ አሳሰበ።
የክለቡ አመራሮች ረቡዕ ዕለት ተጨዋቾችን ሰብስበው ከመከሩ በኋላ ጥቅማጥቅሞችና ደመወዝ ገብቶላችኋል በማለት የክለቡ ፕሬዝዳንት ቢናገሩም ገንዘቡ ሳይገባ መቅረቱ ቅሬታ ፈጥሯል።
ሁኔታው እንዲስተካከል በቃል ሲጠይቅ የነበረው አሰልጣኝ አብርሃም በግልባጭ ለሊግ ካምፓኒውና ለፌዴሬሽኑ ባስገባው ደብዳቤ በዚህ ቅሬታ ውስጥ የሆኑ ተጨዋቾችን ይዤ ውጤት ማምጣት አልችልም ቃል ገብታችሁ አልፈጸማችሁም በዚህ መንገድ ጠንካራ ቡድን መፍጠር አልችልም ወደ ጅማም መሄድ ይከብደኛል በማለት ማሳሰቢያ መስጠቱ ታውቋል።
ከአመራሮቹ ጋር በተካሄደ ውይይት ላይ ኳስ ወደ ኋላ እየመለሳችሁ ነው በማለት ፕሬዝዳንቱ የሰጡት አስተያየት ግርምትን ፈጥሯል። አሰልጣኙ ይሄን ጉዳይ ለኛ ተዉልን የሚመስል አስተያየት ሰጥቷል ተብሏል በአንድ ጨዋታ ከ600 በላይ ፓስ ያደረገው ቡድኔ ነው በማለት ፕሬዝዳንቱን ወረፍ አድርጎል።
- ማሰታውቂያ -
ከዚያም ውጪ በኔ ስልጠናና አጨዋወት የማታምኑ ካላችሁ አሁኑኑ መለያየት እንችላለን በማለት ቆፍጠን ያለ ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። የኔን ገንዘብ አስገቡልኝና ወደ ስራዬ ልግባ የሚል ግለኛ አሰልጣኝ በበዛበት እግር ኳስ አሰልጣኝ አብርሃም የልጆቹን ገንዘብ በቅድሚያ አስገቡ ማለቱም ታውቋል። የአሰልጣኙ ቆራጥ አቋም አስድንግጧቸው ይሁን አይሁን ባይታወቅም አመራሮቹ ለአዲስ ፈራሚዎች ካላቸው የ6ወር ደመወዝ የ4ቱን የነባሮቹን ደግሞ የታህሳስን ደመወዝ በመክፈል ቅሬታውን ለማለዘብ ሞክረዋል። ያም ቢሆን ደስተኛ ያልሆኑ ተጨዋቾች እንዳሉ የተረዳው አሰልጣኝ አብርሃም ከ5ቀን በኋላ ትላንት ተሰባስበው በሰሩት ልምምድ ላይ ሳይገኝ ቀርቷል።
ቡድኑ ዛሬ የኮቪድ 19 ምርመራ በማድረግና ቀለል ያለ ልምምድ በማድረግ ነገ ከሰአት ወደ ጅማ ተጉዞ አርብ 9 ሰአት ወላይታ ድቻን የሚገጥም
መሆኑ ታውቋል። በአስተዳደራዊ ችግር ምክንያት 5ቀን ልምምድ ሳይሰሩ ውጤት ቢጠፋ ሌላ ውዝግብ እንዳይፈጥር ተሰግቷል።