የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት ጅማሮውን ሲያደርግ በቀዳሚነት የተደረገው የአዳማ ከተማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ያለግብ አቻ ተጠናቋል ።
ከጨዋታው በኋላ አስተያየቱን የሰጠው የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የመጀመሪያ የሊጉ ጨዋታቸው ባሰቡት ልክ ባይሆንን መጥፎ አይደለም ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል ።
“ማንኛውም አሰልጣኝ ወደ ሜዳ ሲገባ ለማሰሸነፍ ነው ። እንደ አዲስ ቡድን በምንፈልገው ደረጃ ባንሆንም ግን መጥፎ የሚባል አይደለም ። አጀማመራችን ውስጥ ቀስ በቀስ ወደ ሪትም ውስጥ ለመግባት እየሞከርን የግብ ዕድሎችንም ባሰብነው መልኩ ለመፍጠር እየሞከርን ነበረ ግን ሳንጠቀምባቸው ቀርተናል ።
እንደ ቡድን መሻሻል ያለባቸው ያየናቸው በቀጣይ ማስተካከል ያሉብን መሻሻል ያለባቸው ነገሮች አሉ እነሱን በቀጣይ አሰትካክለን የተሻለ ለመሆን እንጥራለን ።”
- ማሰታውቂያ -
አሰልጣኙ አክሎም በጨዋታው ላይ የተመለከተውን የቡድኑን ጠንካራ እና ደካማ ጎንም እንዲህ ገልፆታል ።
“እኛ በግለሰብ ላይ አልያም የሆነ ዲፓርትመንት ላይ ሳይሆን እንደ ቡድን ነው መጫወት የምንፈልገው ። ስለዚህ ሁሉም ቦታ ላይ ከዚህ የተሻለ በኳስ አጀማመር ፤ መሀል ለይ እንዲሁም በማጥቃት ሶስተኛ ዞን ላይ በቁጥር መብዛት ፤ ሰው ሜዳ ላይ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ መውሰድ መ የተሻለ የግብ ዕድል መፍጠር ከዚህ የተሻለ አሻሽለን ለመቅረብ ነው የምንሰራው ።”