በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን በመልቀቅ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከተቀላቀለ በኋላ ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ ላይ ይገኝ የነበረዉ የመሐል ሜዳ ቴክኒሽያን ዳዊት ተፈራ (ኦዚል) በትላንትናው ዕለት በልምምድ ወቅት ባጋጠመዉ ጉዳት ምክንያት ከጨዋታ ዉጭ መደረጉ ይታወሳል።
ይሄንንም ተከትሎ ተጫዋቹ በዛሬዉ ዕለት ተጨማሪ ምርመራ ተደርጎለት ለ6 ሳምንታት ያህል ከሜዳ እንደሚርቅ ተረጋግጧል።