የተከላካይ አማካዩ ዓለምአንተ ካሳ ኢትዮጵያ ቡናን በመልቀቅ ወደ መከላከያ ማምራቱ ዕርግጥ ሆኖአል።
በተገባደደው የዉድድር አመት ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደግ የቻሉት መከላከያዎች በቀጣዩ አመት በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆነው ለመቅረብ ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል። ከዚህ በተጨማሪም በዛሬዉ ዕለት የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ዓለምአንተ ካሳ ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
ያለፉትን ሁለት የዉድድር አመታት ከቡናማዎቹ ጋር ማሳለፍ የቻለዉ የቀድሞዉ የደደቢት እና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጫዋች ዓለምአንተ ካሳ ከቀጣዩ የዉድድር አመት ጀምሮ በመከላከያ መለያ የምንመለከተው ይሆናል።