የወላይታ ዲቻ ስፖርት ክለብ ሰሞኑን በክለቡ ለተፈጠረዉ ዉዝግብ መነሻ ነው ያለውን የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ወንድሙ ሳሙኤልን ከኃላፊነት አንስቷል።
የክለቡ ቦርዱ ስራ አስኪያጁን ከሀላፊነት እንዲነሳ ሲወስን በሶስት መሠረታዊ ምክንያቶች መሆኑንም የገለፀ ሲሆን ከጥፋቶቹ መካከልም :- አንደኛ የክለቡን የስም ለውጥ በተመለከተ የተጻፈው ደብዳቤ በክለቡ ቦርድ እና የሥራ አስፈጻሚ እውቅና የለለዉ በመሆኑ እና ማስተካከያ ተብሎ የተጻፈው ደብዳቤ በራሱ ስህተት ያለዉ በመሆኑ ምክንያት ስራ አስኪያጁን ለማሰናበት መወሰኑን ቦርዱ ይፋ አድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
በዚህም አቶ ምትኩ ሀይሌ በጊዜያዊነት የክለቡ ስራ አስኪያጅ ሆነዉ እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።