በ2014 የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያውን ዙር 16 ነጥቦችን ይዞ በ13ኛ ደረጃ ያጠናቀቀው የድሬዳዋ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር ተስማምቷል ።
ድሬዳዋ ከተማ የውድድር አመቱን ከአሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ጋር መጀመር የቻለ ቢሆንም ከዘጠኝ ሳምንት በኋላ ግን አብረው መቀጠል አልቻሉም ። ሊጉ ከአስረኛ ሳምንት በኋላ በድሬዳዋ ከተማ ሲደረግ ክለቡን በቴክኒክ ዳይሬክተርነት ሲያገለግሉ የነበሩት ፉአድ የሱፍ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ተሹመው ስድስት ጨዋታዎች ያደረጉ ሲሆን ከነዚህ ጨዋታዎችም በአንዱ ብቻ ድል ነበር ድል ማድረግ የቻሉት ።
የሁለተኛ ዙር ከመጀመሩ በፊት ለቦታው ሁነኛ ሰው ለመቅጠር እንቅስቃሴዎችች ማድረግ የጀመሩት ድሬዳዋ ከተማዎች አሰልጣኝ ሳምሶን አየለን የክለቡ ዋና አሰልጣኝ አድርገው ለመሾም ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ። አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም ሐረር ቢራ ፤ ዳሽን ቢራ ፤ ስሑል ሽሬ እንዲሁም የተለያዩ የብሔራዊ ሊግ ክለቦችን ማሰልጠን ችለዋል ።
የሁለተኛ ዙር ውድድር በአዳማ ከተማ ጅማሮውን ሲያደርግ ድሬዳዋ ከተማ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወላይታ ድቻን የሚገጥም ይሆናል ።