በአሰልጣኝ ዘማርያም ወ/ጊዮርጊስ እየተመሩ የቅድመ ዉድድር ዝግጅታቸዉን በሀዋሳ ከተማ ታደሰ ኢንጆሪ ሆቴል መቀመጫቸዉን በማድረግ እየከወኑ የሚገኙት ድሬ ከተማዎች አውዱ ናፊዑ የተባለ የመሃል ተከላካይ በአንድ ዓመት ኮንትራት ማስፈረማቸዉ ታዉቋል።
ከክለቡ በለቀቁ ወሳኝ ተጫዋቾች ምትክ አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ በመቀላቀል ላይ የሚገኙት ቡርትካናማዎቹ ሁለተኛ የውጭ ዜጋ በማድረግ አውዱ ናፊዑን አስፈርመዋል።
ተጫዋቾቹ ከዚህ ቀደም ለኢኳቶሪያል ጊኒዉ ፉቱሮ ኪንግስ እና ለጋናው ኩማሲ አሳንቴ ኮቶኮ ተጫዉቶ ማሳለፍ ችሏል።