በሁለተኛ ዙር የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ተሻሽሎ ለመቅረብ አዲስ አሰልጣኝ የቀጠረዉ ድሬዳዋ ከተማ በዝዉዉር መስኮቱ ላይ በማሳተፍም አንድ ተጫዋች ወደ ስብስቡ መቀላቀል ችሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት ደግሞ ሁለት ተጫዋቾችን በዉሰት ማስፈረም ችሏል።
ድሬዳዋ ከተማ በከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ከሆነዉ ኢትዮጵያ ንንግድ ባንክ ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረም የቻለ ሲሆን ፤ ብርቱካናማዎቹን የተቀላቀሉት ተጫዋቾችም ከዚህ ቀደም ለሀዋሳ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ መጫወት የቻለዉ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አባይነህ ፌኖ ሲሆን ሁለተኛው ተጫዋች ደግሞ ከዚህ ቀደም ለፋሲል ከነማ እና ጅማ አባጅፋር መጫወት የቻለዉ የመሐል ተከላካዩ ከድር ሀይረዲን መሆናቸው ታዉቋል። ሁለቱም ተጫዋቾች ክለቡን የተቀላቀሉት በዉሰት ዉል መሆኑም ተገልጿል።