ድሬዳዋ ከተማ ወጣቱን የቀድሞ የድሬዳዋ ከተማ ተጫዋች የነበረውን የመሃል ተጫዋች ያሬድ ታደሰን ሲያስፈርም የሁለት ተጫዋቾችን ዉል አራዝሟል፡፡
ባለፉት ሁለት አመታትን ለወልቂጤ ከተማ በመጫወት ያሳለፈው ያሬድ ታደሰ ዳግም ለድሬዳዋ ከተማ ለሁለት ዓመታት ለመጫወት በዛሬው ዕለት ፊርማውን አኑረዋል፡፡
ሌላው አምና ጥሩ እንቅስቃሴ በማድረግ ያሳለፈው ወጣቱ አቤል አሰበ ፕሮፌሽናል ኮንትራት ከቡድናችን ጋር ተፈራርሟል፡፡ በ2014 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጰያን ፕሪምየር ሊግ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ በማድረግ ቡድናችንን በችግር ጊዜ በመሃል ተከላካያ ስፍራ እና በተከላካይ አማካይ ስፍራ ሲጫወት የነበረው አቤል ለሁለት ዓመታት ከድሬ ከተማ ጋር የሚቆይ ይሆናል፡፡
በ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው የመስመር ተከላካዩ ያሲን ጀማልም ከጉዳት መልስ አምና ባሳየው ጥሩ እንቅስቃሴ ክለቡ ውሉን በሁለት አመት ሊያድስለት ቸሏል፡፡ ያሲን ጀማል ወደፊትም ከኢንየው እና አሰጋኝ ጋር የመጀመሪያ ተሰላፊ ለመሆን ብርቱ ፉክክር የሚያደርግ ይሆናል፡፡
- ማሰታውቂያ -
©dire official