ከአሰልጣኝ ዘማሪያም ወ/ጊዮርጊስ ጋር እሰጥ እገባ ውስጥ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ በጊዜያዊነት ሲያሰለጥኑ የነበሩትን አሰልጣኞቹን አሰናብቷል።
በመጀመሪያው ዙር 15 ጨዋታዎች በ16 ነጥብና 9 የግብ ዕዳ 13ኛ ይዞ ያጠናቀቀው ድሬዳዋ ከተማ ቋሚ አሰልጣኝ ለመቅጠር ከጫፍ መድረሱን ተከትሎ ስድስቱን የቡድኑ የአሰልጣኞች ቡድን አባላትን እንዲነሱ በመወሰን ለቀጣዩ አሰልጣኝ በሩን ክፍት አድርጓል።
ክለቡ ከቀድሞ አሰልጣኝ ዘማሪያም ጋር ውዝግብ ውሰጥ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ካልተስማሙ ቀጣዩ አሰልጣኝ በምን ድርሻ ይቀጠር ይሆን ? የሚለው አጓጊ ሆኗል።