የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዲፓርትመንት ዳይሬክተር ለመቅጠር ባወጣው የስራ ማስታወቂያ መሠረት መስፈርቱን ያሟሉ አምስት ተወዳዳሪዎች ባለፈው ሳምንት በጁፒተር ሆቴል ለውድድር የቀረበውን የአንድ ዓመት የእግር ኳስ ልማት እቅድ አዘጋጅተው ገለፃ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
የፊፋ የቴክኒክ አማካሪ ዶሚኒክ ኒዮንዚማ በተገኙበት የተደረገውን ገለፃ ጨምሮ በስድስት የተለያዩ መመዘኛዎች (የስራ ልምድ ፣ የአሰልጣኝነት ላይሰንስ ፣ የትምህርት ዝግጁነት ፣ የእቅድ አዘገጃጀት ፣ የእቅድ አቀራረብና ጥያቄዎች የመመለስ ችሎታ እና ቃለ መጠይቅ) ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች ተለይተው ታውቀዋል። በዚህም መሠረት
1ኛ – (ተመራጭ) – አቶ ዳንኤል ገብረማርያም
2ኛ – (ተጠባባቂ) – ዶ/ር ጌታቸው ቂናጤ
3ኛ – (ተጠባባቂ) – አቶ ዮሐንስ ሳሕሌ ሆነዋል።
በውጤቱ መሠረት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት አቶ ዳንኤል ገብረማርያም በእግር ኳስ ሁለተኛ ዲግሪ ባለቤት ሲሆኑ የካፍ A ላይሰንስ ያላቸውና በተለያዩ ክለቦች የስራ ምልድ ያላቸው እንዲሁም በካፍ ኢንስትራክተርነት የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ባለሙያ ናቸው።