የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሸሰን 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሲምፖዚየም በአሁኑ ሰዓት በአርባምንጭ ኃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።
መርሐ ግብሩም በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጂራ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን ከዚያ በመቀጠልም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ፍራንኮ በፌዴሬሽኑ ስኬቶች ፣ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ ጥናዊ ፅሁፍ ቀርቧል። በፅሁፉም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በክለብ ደረጃ ፣ በማህበራዊ ዘርፍ ፣ በመንግሰት ፣ በሚዲያ ፣ በባለሙያዎች ፣ በደጋፊዎች እና አጋር ድርጅቶች ዘርፍ ያሳካቸዉን ነገሮች በዝርዝር ማብራሪያ የሰጠባቸዉ ሲሆን ከተጠቀሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከልም :-
° የፓይለት ከ15 አመት በታች ፕሮጀክት መቋቋሙ ፤
°ብሔራዊ ቡድኑ በሀገር ዉስጥ አሰልጣኝ መመራቱ ፤
° ብሔራዊ ቡድኑ ከሀገር ዉጭ ሲጫወት ከወትሮው በተለየ ጥሩ ተፎካካሪ መሆኑ ፤
° የሪፎርም ስራ መሰራቱ ፤
° ከ20 አመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሴካፋ ላይ ሻምፒዮን መሆኑ ፤
° ከ17 አመት በታች የሴካፋ ዉድድር ላይ ብሔራዊ ቡድኑ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ፤
- ማሰታውቂያ -
በክለብ ደረጃ
° የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎችበ DSTV እንዲታይ መደረጉ ፤
° ከኳሱ ገቢ ማግኘት መቻሉ ፤
° ለስታዲየም መስሪያ ክለቦች የቦታ ይዞታ ባለቤት መሆናቸው ፤
በመንግሥት ደረጃ
°ስታዲየሞች መሰራታቸውን ባይጠናቀቁም ፤
° የማሰልጠኛ ተቋማት መከፈት ፤
በሚዲያ ዘርፍ
°የሬዲዮ እና ቴሌቭዝን መበራከት
° የሶሻል ሚዲያ መበራከት ፤
° ከፌዴሬሽኑ ጋር ተባብሮ የመስራት ፤
በባለሙያዎች ዘርፍ
° ከፌዴሬሽኑ ጋር ይበልጥ ተቀራርበው የመስራት ፤
° ባለሙያዎች ለተጫዋቾች እና ዳኞች መብት መጠየቅ መቻላቸዉ ፤
° ከአቻ ፌዴሬሽኖች ጋር በትብብር መስራት መቻል ፤
° ማህበራትን ማቋቋም ፤
በደጋፊዎች ደረጃ
° ሰላማዊ የድጋፍ ስርዓት ፤
° የደጋፊዎች ቁጥር መበራከት ፤
° የደጋፊ ማህበራት መቋቋም ፤
በአጋር ድርጅቶች ዘርፍ
° ምርት እና አገልግሎታቸውን በፌዴሬሽኑ በማስተዋወቅ ተደራሽ መሆን ፤
° ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣት እና የመሳሰሉት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ከቀረቡት እና በፌደሬሽኑ በኩል ስኬት ተብለዉ ከተመዘገቡት መካከል ይገኙበታል።
በመቀጠል ከዚህ ቀደም ከነበሩት ተግዳሮቶች ተብለው በጥናታዊ ፅሁፉ ተከቀመጡት መካከል ደግሞ :-
° የክለቦች አደረጃጀት የካፍን እና የፊፋን መስፈርት ማሟላት አለመቻል ፤
° የተጫዋቾች አያያዝ ክፍተት ፤
° የፋይናንስ ዕጥረት ፤
° እድሜን መሰረት ያደረጉ ዉድድሮች አለመኖር ፤
° ፌዴሬሽኑ አካዳሚዎችን ያለመቆጣጠር እና ፈቃድ ሰጪ አለመሆን ፤
° በቂ የስፖርት ማዘውተሪያ አለመኖር ፤
° የስታዲየሞች የካፍን እና የፊፋን መስፈርት አለሟሟላት ፤
በክለብ ደረጃ
° የክለቦች የአደረጃጀት ችግር
የፋይናንስ ግልፀኝነት አለመኖር
የአመራር ክፍተት ፤
° የቴክኒክ ባለሙያዎች አለመኖር ፤
° ታዳጊዎች ላይ ያለመስራት ፤
° የክለቦች መፍረስ ፤
° በዕቅድ የመመራት ችግር ፤
በሚዲያ ዘርፍ
° የተዛባ ዘገባ ፤
°ስሜታዊነትን ያዘለ ዘገባ ፤
° ደጋፊን የመከፋፈል አዝማሚያ ፤
° የግለሰብን ጥቅም የማስቀደም እና የመሳሰሉት ፌዴሬሽኑን ካጋጠሙት ተግዳሮቶች መካከል በጥናታዊ ፅሁፉ ላይ የተገሉፁ ሲሆኑ ፤ በጥናታዊይ ፅሁፋ ላይም በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎች በአራት ቡድን ተከፍለዉ ዉይይት ያደረጉ አድርገዋል።
ከዉይይታቸዉ በኋላ ካነሷቸዉ ነጥቦች መካከልም ፈረዴሽኑ ሙሉ ለሙሉ አሰራሩ መዘመን እንደሚገባው እንዲሁም የተለያዩ አቅም ያላቸዉ ባለሙያዎች በፌዴሬሽኑ እንዲካተቱ የተጠቆመ ሲሆን ፤ ከዚህ በተጨማሪም ፌዴሬሽኑ የክለቦችን ገንዘብ አያያዝ እንዲሁም አደረጃጀት እንዲፈትሽ ተጠቁሟል።
ሚዲያዎችን በተመለከተም ለከፍተኛ ሊግ እና አንደኛ ሊግ በቂ ትኩረት እንዲሰጡ የተጠቆመ ሲሆን ፤ ከCOVID ጋር ተያይዞም ትክክለኛ እና ተአማኒነት ያለዉ ምርመራ እየተደረገ እንዳልሆነ በተጨማሪም በዳኞች በኩል የአቅም ዉስንነት እንዳለ ተዎያዮቹ አንስተዋል። የተወያዮቹን ሀሳብ ተከትሎም የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ የማብራሪያ ሀሳብ ሰጥተዋል።