” የሀረሪ ክልል የሰጣቸውን ውክልና ማንሳቱ ተቀባይነት የሌለውና ህጉን ያልተከተለ በመሆኑ በምርጫው ላይ እንደምሳተፍ ርግጠኛ ነኝ” ሲሉ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ተናገሩ።
የሀረሪ ክልል ክልሉን ወክለው በስራ አስፈጻሚነት የሚወዳደሩ ዕጩዎች ባቀረቡት ተቃውሞ በፕሬዝዳንትነት እንዲወዳደሩ የወከልናቸውን የአቶ ገዛኸኝ ወልዴ ውክልና አንስተናል” ማለቱን አቶ ገዛኸኝ ወልዴ ተቀባይነት የሌለውና የምርጫ ህጉን ያልተከተለ በማለት ውድቅ አድርገውታል።
አቶ ገዛኸኝ ሲናገሩ” መቶ ፐርሰንት ርግጠኛ ነኝ …እወዳደራለሁ የምርጫው ቀን ትላንትም ተጠናቋል ቀን የተጨመረው መላክ ላልቻሉ ክልሎች ዕድል ለመስጠት እንጂ ለሌላ አይደለም ሀምሌ 7 ውክልና ሰጥተው አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያት ሀምሌ 19 ውክልና አንስቻለሁ ማለት አይችሉም ከምርጫ አስፈጻሚው ተገቢ የሆነ ምላሽን እፈልጋለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ገዛኸኝ እንዳስረዱት “የዛሬ አራት አመት ትግራይ ክልል አቶ ተስፋዬ ካህሳይን ወክሎ ባለቀ ሰአት ውክልናዬን አንስቻለሁ ሲል በወቅቱ የነበረው አስመራጭ ኮሚቴ አልተቀበለውም አሁን ካለው የምርጫ አስፈጻሚም ተመሳሳይ ምላሽ እጠብቃለሁ” ሲሉ ገልጸዋል።