“ምርጫው ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ ከተሸነፍኩ ካሸነፈው ጋር ሆኜ ኳሱን አግዛለሁ በሸፍጥ ከሆነ የማጋለጥ ስራ እሰራለሁ ከኳሱ ግን መቼም አልርቅም”
አቶ መላኩ ፈንታ
/ ከሶስቱ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ
ተፎካካሪዎች መሀል አንዱ/
“9ቁጥር ላይ እንድጫወት ዳኛ ወይ አሰልጣኝ እንድሆን አይጠብቅብም የምርጫ ፉክክሩን አቋርጦ ይወጣል ጊዜ የለውም የሚለውም ውሸት ነው በፍጹም ራሴን አላገልም” ሲሉ አቶ መላኩ ፈንታ ተናገሩ።
ከሶስቱ የፌዴሬሽኑ የፕሬዝዳንትነት ተፎካካሪዎች መሀል አንዱ የሆኑት አቶ መላኩ ለመገናኛ ብዙሀን ዛሬ ጠዋት በሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ምርጫው ፍትሃዊ መሆን እንደሚኖርበት ፍትሃዊነትም መለመድ እንዳለበት አስረድተዋል። “የማንም የፖለቲካ ድርጅት አባል አይደለሁም በግሌ የምፈልገውን ለማሳካት ማንኛውንም ሰው አሳምኖ የማሰራት አቅም አለኝ
ከምርጫ ፉክክሩን አቋርጦ ይወጣል ጊዜ የለውም የሚለው ውሸት ነው በፍጹም ራሴን አላገልም ነገር ግን ምርጫው ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ተካሂዶ ከተሸነፍኩ ካሸነፈው ጋር ሆኜ ኳሱን አግዛለሁ በሸፍጥ ከሆነ የማጋለጥ ስራ እሰራለሁ ከኳሱ ግን መቼም አልርቅም” ሲሉ መልሰዋል።
- ማሰታውቂያ -
” ምርጫ ሲካሄድ ክርክርና ሀሳብን በነጻነት መግለጽ እንደሌለ፣ የተገባው ቃልም ተፈጸመ ወይስ የሚል ገምጋሚ እንዳልነበር ምርጫው በገንዘብና በኔትወርክ የሚሰራ ሚዲያው ለወገነው ወገን የሚያደላበት በአጠቃላይ ምርጫው ለማስተጓጎል ድምጽ ሰጪ ገንዘብ የሚቀበልበት መሆኑን የታዘብነው ነው ይህን ለማስወገድ የምችለውን አደርጋለሁ” ያሉት አቶ መላኩ
“የምርጫው ሞቶ ለመለ’ ወጥና ለመለወጥ የሚል ነው
120 ሚሊዮን ህዝብ አለን የኛ ህዝብ ደግሞ ሀብታችን ነው ዋናው ግባችን የሚሆነው የመጀመሪያው ፌዴሬሽኑን የመፈጸም አቅም መገንባት፣ የተጀመሩ በጎ ነገሮችን ማስቀጠል የጎደሉ ነገሮችን መሙላት፣ የህግ የአሰራርና የአደረጃጀት ማሻሻያ ማድረግ፣ በብቁ ባለሙያ እንዲደራጅና ተከታታይ የሆነ አቅም ግንባታ ማካሄድ፣ ማበረታቻና ተጠያቂነት ያለው ፤ ሁለተኛው ፌዴሬሽኑና ክለቦቹን በገንዘብ ማጠናከር የፋይናንስና የኦዲት አሰራሮችን ማጠናከር፤ ሶስተኛው የመሠረተ ልማት ላይ አተኩረን የካፍ መመዘኛ የሚያሟላ ስታዲየም ባለመኖሩ የተሰደደውን ብሄራዊ ቡድን ለመመለስ እንጥራለን” ሲሉ አስረድተዋል።
አቶ መላኩ በሂልተኑ የምርጫ ዘመቻቸው ላይ እንደተናገሩት “ምንም አይነት ወንጀል አልሰራሁም ከሰሱኝ ምክንያት ሲጠፋና ለውጡ ሲከሰት ተፈታሁ የምርጫው ህግ የሚከለክለው በሙስና የተቀጣውን ነው እኔ ግን አልተቀጣሁም ህጉ አይከለክለኝም በአለም ላይ አራት አይነት ዳኝነት አለ አንደኛው የፈጣሪ ዳኝነት ነው ዋናው ይሄ ነው ይሄ ዳኝነት አይካዳችሁ እኔን ፈጣሪ ጠብቆኛል ለዚህ ነው እንደወጣሁ ወደ ተቋም መገንባት የገባሁት፤ሁለተኛው የህዝብ ዳኝነት ነው ሌባ ስላልሆንኩ በህዝቡ መሃልና የትም ስሄድ ቀና ብዬ የምሄደው ለዚህ ነው፤ሶስተኛው የህሊና ዳኝነት ነው እኔ ምንም ህሊናዬን የሚቆረቁር ነገር አልሰራሁም፤አራተኛው
የመደበኛ ፍ/ቤት ዳኝነት ነው ፍትህን አስፍኖ ባይለቀኝም ምንም ስላልሰራሁ ለውጡ ሲመጣ ተለቀቅኩ” ሲሉ የግል ዕምነታቸውን አስረድተዋል።
” ወደ ካፍና ፊፋ ለመጓዝ ስል የፌዴሬሽኑን ፕሬዝዳንትነት ቦታ መሸጋገሪያ አላደርግም የሚወራው ሁሉ ውሸት ነው መሸጋገር ብፈልግ ሌሎች ቦታዎችን እሞክር ነበር ነገር ግን እንደሌሎቹ የራሴን ሌጋሲ ማስቀጠል ሀገሬና ኳሷ ተቀይራ ማየት እፈልጋለሁ በመላው ህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቅሙን ያጠናከረ ፌዴሬሽን መፍጠር ነው ዋናው ተልዕኮዬ” ያለው አቶ መላኩ “በድምጻቸው የመምረጥ መብቱ ያላቸው የጠቅላላ ጉባኤው አባላት በዓላማና ይዘን በመጣነው ሀሳብ እንጂ በሚቀበሉት ገንዘብ ምርጫ እንዳያደርጉ እጠይቃለሁ ገንዘቡ ካስፈለገ ደግሞ ገንዘቡን ተቀብሎም ቢሆን ለሀገር የተሻለ ነገር የሚሰራውን እንዲመርጡ አደራ እላለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።
ለእግርኳስ ቅርብ አይደሉም ማረሚያ እያሉ እስረኞቹ ሲጫወቱ ረበሹኝ ብለው ከሰዋል የተባሉት አቶ መላኩ በሰጡት ምላሽ ” ታስሬ የነበርኩበት ቦታ በማረሚያ ቤቱ ኋይት ሀውስ ተብሎ ይጠራል ቦታው ጠባብና ጥበቃ ያለበት ቤተሰብሁሉ በደንብ ማግኘት የማንችልበት ቦታ ነው እኔ አስክንድር ነጋ አንዷለም አራጌን ጨምሮ ከግንቦት ሰባት ጋር ተያይዞ የታሰሩ ሰዎች ጋር አምስት ሆነን የታሰርንበት ነው ከሌሎቹ እስረኞች ጋር አንገናኝም ሰው ከሰው አንገናኝም አንረብሽም ነበር ምናልባት የሌሎቹን እስረኞች መብት እያየን እንቀና ነበር እንጂ” ሲሉ አስተባብለዋል።
የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤና ምርጫ በተያዘለት ቀን የሚቀጥል ከሆነ የፊታችን ቅዳሜና አሁድ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል