የሴቶች ፣ የከፍተኛ ፣ አንደኛ እና ከ20 ዓመት በታች ሊጎች የዝውውር ጊዜ የሚጀመርበት ወቅት ታውቋል
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስር የሚከናከኑ የሴቶች ፕሪምየር ሊግ ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ ፣ የወንዶች አንደኛ ሊግ እና ከ 20 ዓመት በታች ሊግ ክለቦች የዝውውር ጊዜ ታውቋል።
የውድድር ዳይሬክቶሬት ለተሳታፊ ክለቦች በላከው መረጃ የሁሉም ሊጎች የዝውውር ጊዜ ጳጉሜ 4/2014 ተጀምሮ እስከ ሕዳር 15/2015 እንደሚቆይ አስታውቋል።
በተጨማሪም ክለቦች ለቡድኖቻቸው ከዘር እና ሀይማኖት ነፃ የሆነ ስያሜ እንዲሰጡ እና መሟላት የሚገባቸውን የዝውውር መስፈርቶች አባሪ በማድረግ ከወንዶች ከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪዎች በቀር 10,000 ብር ክፍያ በመፈፀም (ለወንዶች ከፍተኛ ሊግ 20 ሺህ ብር) እንዲመዘገቡ አሳስቧል።