ጅማ አባጅፋር በሀዋሳ ከተማ በተረታበት ጨዋታ በቀይ ካርድ የተሰናበተው የጅማ አባጅፋሩ ዳዊት እስጢፋኖስ ላይ ቅጣት ተላለፈ።
ሀዋሳ ከተማ ከጅማ አባጅፋር ጋር ባደረጉት የሊጉ የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ ላይ ተቀይሮ ወጥቶ ተጠባባቂ ተጨዋቾች በሚቀመጡበት ቦታ ላይ እያለ አንድ ኳስ አቀባይ ሰአት እየገደለ ነው በሚል በውሃ ላስቲክ መምታቱና በህጉ መሠረት በቀይ ካርድ ሲወጣ የጨዋታ መሪዎችን አስጸያፊ ስድብ መሳደቡን በዳኞችና በኮሚሽነሩ ሪፖርት ቀርቦበታል ሲል የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ገልጿል።
በዚህም መሠረት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 63 እና 66 ኳስ አቀባይ በማታት እና ዳኛን አፀያፊ ስድብ በመሳደብ 7 ጨዋታና 7ሺህ ብር መቀጣቱን አስታውቋል።