የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ ዋልያ ቢራ ጋር ያለውን ስምምነት ለተጨማሪ ዓመታት አራዝመዋል ።
በሸራተን አዲስ እየተካሄደ ባለው የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለአራት አመታት የሚቆይ ስምምነት ከ ዋልያ ቢራ ጋር ፈፅመዋል ።
የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ ዋልያ ቢራ ጋር የገባውን የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ተከትሎ በአራት አመት የሚከፈል 62 ሚልዮን ብር እንደሚያገኙ ተገልጿል ።
ይህም የገንዘብ መጠን ከዚህ ቀደም ዋልያ ቢራ ጋር ከተፈፀመው በ ስድስት ሚልዮን ብር ከፍ ያለ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ተናግረዋል ።