አዲስ አዳጊው ኢትዮ ኤሌክትሪክ የአሰልጣኙን ክፍሌ ቦልተና ውል ካራዘመ በኋላ ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል ።
በዛሬው ዕለትም አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን የአንድ ነባር ተጫዋች ውልንም አራዝሟል ።
ጌቱ ሀይለማርያም ( ከሰበታ ከተማ ) ፤ ሀይሌ ገብረትንሳኤ ( ከኢትዮጵያ ቡና ) ፤ ተስፋዬ በቀለ ( ጃምቦ ) እና ግብ ጠባቂው ፍቅሩ ወዴሳ ( ከሲዳማ ቡና ) ኢትዮ ኤሌክትሪክን የተቀላቀሉ ተጫዋቾች ናቸው ።
የቀድሞው የብሔራዊ ቡድን ተጫዋች እና ከሶስት የተለያዩ ክለቦች ጋር የሊጉ ሻምፕዮና መሆን ችሎ የነበረው ምንያህል ተሾመ በቡድኑ ለተጨማሪ አንድ አመት በክለቡ ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል ።