ዶክተር አሸብር ስልጣኔን አለቅም አሉ…
” የኤርፖርቱ ተቃውሞ ድራማ ነው ለዚህ ደግሞ መቶ ሺህ ብር ተከፍሏል መረጃው አለን”
“ዶክተር አያሌው ጥላሁን ወንጀል ሰርቷል በህግ መጠየቅም አለበት”
- ማሰታውቂያ -
ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ
የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት
“በቶኪዮ ኦሎምፒክ ህዝብና መንግስት የለፋበትና የጠበቀውን ያህል ውጤት ባለመገኘቱ አዝነናል ይቅርታም እንጠይቃለን”ሲል የኢትዮዽያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገለጸ።
የኮሚቴው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ማንም ማንም ላይ ጣት ሳይቀስር ውጤቱ በምንፈልገው ደረጃ ባለመሳካቱ ይቅርታ እንጠይቃለን ብሏል።
ውጤት መጥፋቱን በተመለከተ ምክንያት የነበረውን ጉዳይ ሲዘረዝር “የመንግስት አካል የትግራይ አትሌቶችን በተመለከተ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንዳያሳትፍ መመርያ ሰጥቶ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ባለመቀበሉ አትሌቶቹን አሳትፏል ያም ሆኖ በዚህ ክርክር ምክንያት በአትሌቶች ላይ የደረሰው የሞራል ስብራት ትልቅ ጉዳት አምጥቷል። ከዚህ ውጪ የግሎባል ማርኬቲንጉ ከህክምና ቡድኑ ጋር ተመሳጥሮ ሸፍጥ መስራቱና ከዶክተር ወልደ መስቀል ኮስትሬ በኋላ በኢትዮዽያ የብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ አለመኖሩ ኢትዮዽያን ጎድቷል” በማለት ኮሚቴው ገልጿል።
በቶኪዮ ኦሎምፒክ መክፈቻም መግቢያ የተሰጣቸው 6 ኦፊሺያሎች አስቀድመው መዘጋጀት ሲኖርባቸው በማርፈዳቸውና በሰአቱ ባለመገኘታቸው ስታዲየም ውስጥ ሳይገቡ መቅረታቸውንና ሀገራችንን መወከል አለመቻላቸውን ኮሚቴው ገልጾ ያም ሆኖ የሚጠበቅብንን ያህል ህዝባችንን መጥነናል ብለን ስለማናምን ይቅርታ እንጠይቃለን” ብሏል ኮሚቴው።
በዚህ መግለጫ ላይ የህክምና ቡድኑ መግለጫ የሰጠ ሲሆን ከቶኪዮ ጉዞ በፊት ስለነበረው ዝግጅትና ቶኪዮ ላይ የገጠመውን ሂደት በዝርዝር አስቀምጠዋል።
ዶክተር አሸብር ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ስለ መክፈቻ ፕሮግራሙ “ስድስቱ ኦፊሺያሎች ቢደርሱም እንደሌላው ጊዜ አንገንም ምክንያቱም 6 ቁጥር ብቻ ነው ያለን” ሲሉ ገልጸዋል።
ከውሃ ዋና ፌዴሬሽን ጋር ተያይዞ “ቤታችሁን ፈትሹ የማይረባ ነገር እንድናወራ አትገፋፉን ወደ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አታምጡት ችግሩ ይፈታ ከቀነ ገደቡ በፊት ጸሃፊው ዝርዝር ማምጣት ሲችል ባለመምጣቱ የተፈጠረ ነው ችግሩ የኛ አይደለም ራሳችሁን ፈትሹ ያሉት ዶክተር አሸብር ” ወደ ኤርፖርት መምጣት የሁሉም መብት ነው አትሌቱ ማን ጠርቶት ነው የሄደው? ማን መቼ እንደሚሄድ ተገልጾ ባለበት ሂደት ቲኬትና ፓስፖርት ሳይዝ ለምን ሄደ.. ይሄ ስም ማጥፋት ነው…ሌላው የተመለሱት ዶክተር አያሌው ጥላሁን ናቸው ገና በወንጀል ይጠየቃሉ በግላቸው ከህክምና ኮሚቴው ጋር ሳይነጋገሩ ነው የወሰኑት… ይሄ ወንጀል ነው አትሌቷ ላይ ችግር ለመፈጠሩ ችግሩ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ነው ይሄ ገና ብዙ ቦታ ይደርሳል” ሲሉ ተናግረዋል።
ሃላፊነት ስለ መልቀቅ የተጠየቁት ዶክተር አሸብር ለጠየቃቸው ጋዜጠኛ “አንተ ቀድመህ ትለቃለህ እንጂ እኔ ሀላፊነቴን አለቅም” በማለት ተናግረዋል። ዶክተር አሸብር “በውጤቱ ደስ ብሎናል የትግራይ አትሌቶች ቢወጡ ኖሮ ውጤቱ ከዚህ የባሰ ይሆን ነበር” ሲሉም አስረድተዋል።
ስለ ኤርፖርት ቃውሞው የተጠየቁት ዶክተር በሰጡት ምላሽ “የኤርፖርቱ ተቃውሞ ድራማ ነው 100 ሺህ ብር ተከፍሎ ነው ተቃውሞው የጠበቀን…
ይህን ያስተባበረው የኢቢሲ ጋዜጠኛም አለበት ከናንተ ጋርም የተባበረ አለ ችግር ካለ መነጋገር ይቻላል ገንዘብ ሰጥቶ ስድብ ግን ልክ አይደለም” በማለት መልሰዋል።
“ይቅርታ የጠየቅነው የተጠበቀውን ያህል ውጤት ባለማምጣቱ ነው በኛ በኩል ግን የምንችለውን ሰርተናል አትሌት የለንም አንሮጥም አሰልጣኝ የለንም አናሰለጥንም ሀገር ዝቅ አለ የተባለው ዝቅ አላለም ይሄ ልክ አይደለም ዝቅ ያደረገን ኮቪድ እንጂ እኛ አይደለንም ባንዲራችንም ከፍ ብሏል የተለየ ነገር የለውም” በማለት ተናግረዋል